Sunday, 21 January 2018
Wednesday, 17 January 2018
-------የስላቅ ዋ ! ዜማ İİ----------
----------//----------------
እንኳን አደረሰህ--- አትበይኝ ፍቅሬ----እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል --- የደማው ውስጠቴ---- የቆሰለው ቁስሌ፡፡
-------//-----------
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን ደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
---------*****----------
(ስሚኝማ ውዴ)
እንኳን አደረሰህ--- አትበይኝ ፍቅሬ----እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል --- የደማው ውስጠቴ---- የቆሰለው ቁስሌ፡፡
-------//-----------
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን ደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
---------*****----------
(ስሚኝማ ውዴ)
ለዘመኑ ብስራት ---- በባዕል ዋ! ዜማ
ባልነበረ ታሪክ --- ግፋቸው ሲሰማ
መድፍ ይተኩሳሉ----በመለከት ፋንታ
ለድንበር የሚሞት-- ወታደር ይመስል-- የጦር መሪ ጋንታ
(---ከ
------ዚ
---------ያ ----ይቀጥላል)
በማታለል ዘዬ----- በቸከ ቅላፄ
ዘወትር ሲያላዝን -----ደም የዋጠው አፄ
ለጀብጀቦ አጎብዳጅ------ ለቸከ ህሌና
መድፍ እየተኮሱ------ ሊያደርቁን ነውና፡፡
---//-----
(አይገርም የኔ ውድ!!)
ግዳይ እንደጣለ--- እንደ አባይ ልጅ አዳኝ
እንደ አባ ታጠቁ--- እንደ አንበሳ ገዳይ
ሊላዝንብን ነው-- ባላየነው እውነት-- በማይገባን ዜማ
በማታለል ቅኔ --በለበጣ ቃላት----- ልባችን ሊደማ፡፡
(ተመልከች የኔ ውድ)
የደርሶ መልስ --አመት መከራ--- ሊያበስረን
የበግ ደም ሰውቶ-- በየአደባባዩ---- እንቁ ጣጣሽ ሊለን
ካራውን ይስላል------በጎቹን ሰውቶ--- ለበጎች ሊየበላን፡፡
(ይ*ታ*ይ*ሽ* እንግዲ----)
የበግ ስጋ ለበግ-- በየትኛው ሀገር -- ተ-በ-ል-ቶ ያውቃል
ማንስ ይሄን አ’ርጎ---ለህዝበ አዳም ልጆች--- አስደስቶ ውሏል
ባላየነው እውነት ባልሰማነው ዜማ ሀሴት ይስተጋባል???
*********//*********
(ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ)
እንኳን አደረሰህ ---አትበይኝ ፍቅሬ-----እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል -- የደማው ውስጠቴ--- የቆሰለው ቁስሌ
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን አደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
(ምክንያቱም---- ውዴ)
ዋ! ዜማን ደግሰው ----ለአዲስ አመት ብስራት
እየተሳለቁ ------በሞተ ማንነት
አድምጡ ይሉናል--- ቅኝት አልባ ዘፈን
ቁና ሙሉ ስቃይ--- መከራን ሲያበስሩን
ደስታነው ብለው-- ዋ!ዜማን ሲነግሩን
******///********
እና ‘ሄን እያየሽ--- የምን መልካም ዘመን--- የምን አዲስ አመት
ለገደሉት ውስጤ ------ሞት ሲደገስለት?
(ምን አልባት የኔ ውድ)
ኤልያስ ከመጣ----- ደመና ተላብሶ
የነሱን ዋ!! ዜማ---- ድግስ አስቀይሶ
አዲስ ዘመን ካየን--- ከሞታችን ጀርባ
ያን ጊዜ ትያለሽ------- በተቀኜ ዜማ
ምን አልባት የኔ ውድ
ዝናቡ ካባራ ------ደምን የሚያዘንበው
መድፉን በመለከት----- ቀይሮ ካየነው
አዲስ አመት መባል------ ለኔ ያን--- ጊዜ ነው፡፡
(ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ)
እንኳን አደረሰህ ---እንዳትይኝ ዛሬ -እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል -- የደማው ውስጠቴ--- የቆሰለው ቁስሌ
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን አደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
(ዜዶ ነኝ የብእር አይኖች ከፈቱ)
Tuesday, 16 January 2018
ወደማርስ ልሄድ ነው
ገመና ሼፋኜን ቤቴን ልስራ ባለ……ህግ ከተላለፈ
መዝግቡኝ ናሳዎች ….ወደማርስ ልሄድ ነው
ከምድር አልችልም ….መሬት ለመንግስት ነው!!!
‹‹‹‹‹‹‹‹‹እዩት ይሄን ዘማኝ!!!!!
ፍርድ ሲገመድል…… ስልጣኑን ሲጋፋ
መሬት ከፈጣሪ የሚለዉ ቀረና ……መሬት ለመንግስት ነው ብሎልህ አረፋ İİ
አፈር እና ውሃ……… አየርና ፀሐይ
እኩል የታደለን ……ቢሆንም ከእርሱ ላይ
ዛሬ ፈረሰና ……ታሪክ ተቀየረ
ከመንግስት ሆነና ……ካምላክ ሚለዉ ቀረİİ
ከወንዙ ዳርቻ ‹‹‹‹ከፎቁ ታዛ ስር›››››
ከነገመናዋ የቀባኋት ምርጊት…… የቆመች በአፈር
በቀን የመጣ ጅብ ……ገፍቶ ካፈረሳት
ኧረ እናቴ ትሙት!!!!! ሚስቴንም ይዉሰዳት İİ
ወገን ከወገኑ……… እየተበላላ
ሰው ከስልጣኑ ጋር…… ሁሌ እየተጣላ
ቂም የነገሰባት …… ባቢሎን ሆነናል
በጥንስስ አለም ላይ…… ተንጋለን ወድቀናል፡፡
የቦለቲካ መርዝ…. በዲስኩር ተገምዶ
እልፍ ዘመን ሲያልፍ……ብዙ ዘመን ሄዶ
‹‹‹አፍላጋት ወረሰን›››… አብዮት ፈነዳ
የደም ጎርፍ ወሰደን …..ምድር ገባች እዳ
ሰማይ እንደጣራ… ዝቅ አለ ተከፍቶ
በዝናቡ ፋንታ …..የሰዉን ደም አይቶ
‹‹‹‹‹‹‹እዩት ይሄን ዘማኝİİİ
በኪነት ምህዳር……. ያልታጠነዉ ጣዖት
ያ’ብሮነት ገበታ …ያስጠላዉ ተሩፋት
እንደአለማወቁ …ቀድሞ በማወቁ
ጭካኔን አንግሶ ….ፍትህን ማራቁ፡፡
ስለዚህ ወገኔ!!!!!!
ህግ እንደተርጔሚዉ….. ተብሎ ከተፃፈ
ገመና ሼፋኙን ቤቴን ልስራ ባለ ……..ህግ ከተላለፈ
ተሰነባበቱኝ ወደማርስ …..ልሄድ ነው
ከምድር አልችልም….. መሬት ለመንግስት ነው፡፡
እዩት ይሄን አዳም!!!!! ፍርድ ሲገመድል ስልጣኑን ሲጋፋ
ባልተፈቀደለት…. በበለስ ሲጠፋ
‹‹‹‹የገነት ዉሃ ልጅ የአባይ ልጅ ሲገፋ››››
መሬት ከፈጣሪው የሚለውን ፍቆ መሬት ለመንግስት ነዉ ብሎልህ አረፋİİİİİİ
ህግ እንደተርጔሚዉ…. ነዉ ከተባባሉ
መንግስት ማለት ህዝብ ቢሆንም ግን ቅሉ
እንግዲህ ተርጉመዉ ‹‹‹አንተ ባለቅኔ ›››
እያመድህ ያለኸ በበረሀዉ ጠኔ
(ዘላለም በላይነህ)
ዝክረ ቴዎድሮስ
፠፠፠ የተኮሳተረ አገሩን የሚያልም፥ ተስፋ የገመደ ግንባር ይታየኛል፡፡ እንደራሱ ጸጉር ነፍጥና ጀግነነት፥ ወኔና ወንድነት አጣምሮ ገምዷል፡፡ ሎሚታ ያስጌጠው የእሳት ጎራዴ ፥ ካፎቱ ተመዝዞ ከሰገባው ወጥቷል፡፡ እሳት የሚተፋ ሽጉጡን በሽንጡ፥ በወገብ ሸጉጧል፡፡ ስልጣን የተራበ፥ ይሁዳ አሰፍስፎ በባንዳነት ወጉ፥ ክብሩን አሳልፎ በባዕዳን ጉቦ ፥ወንድሙን የሚሸጥ ፥ መቅደላን ከቧታል ቀኙን የሚተካው ፊታውራሪ፥ ገብሬ ህያው አሸልቦ ባንዳ ባሰለፈው በእንግሊዝ፥ ሰራዊት ቴዎድሮስ ተከቦ በራሱ ሊወስን ፥ወንድ አንድ ሰው ቆሟል (ውሳኔ ቴዎድሮስ) ‹‹ለጠላት ክንዴን ሰጥቼ፥ ኢትዮጵያን ከማዋርዳት ! የከበረችው ሀገሬን ፥በቁም መሞቷን ከማዬት ! እኔ ልቅደማትና ፥ትውልድ ወንድነት ይማር ! እንዲሰጥ ይረዳሉና ፥የንጉስ ነፍሱ ለሀገር ፡፡ እሳቱ ክንዴን ጨብጠው ፥ ዘላለም ከሚፎክሩ! አሩሩን ልጉረሰውና ይከበር ያበሻ ክብሩ ፡፡ ›› አለና ካሳ ወሰነ ምንም ፍርሃት ሳይገደው እሳቱን ባፉ ጎረሰ ፥ወንዱ ወንድነት ሲገባው (ቀጥሎ!) አንድ ኢትዮጵያ የሚል ፥አንድ ጀግና ወድቋል የለበሰው ልብሱ ፥በደም ተጨማልቋል ሱሪ የታጠቀ ወንድ አንድ ሰው ሞቷል፡፡ ነፍጠኝነት ዘሩን፥ ሀበሻዊ ክብሩን ኢትዮጵያዊ ደሙን ፥ በደሙ ገምዶ መቅደላ መኻል ላይ ለራሱ ሳይሰስት ካሳችን ተማግዶ ከአፈሙዝ በወጣ በገዛ ሽጉጡ ወደቀ ቴዎድሮስ በጁ እሳት ነዶ፡፡ (ቀጠለ!) ባንዳ ያሰለፈ ፈረንጅ አሰፍስፎ ሊማርክ ሲጠጋ ቴወድሮስን ጠልፎ መቅደላ ሲገቡ ንጉሱ ካለበት የወንዶች ወንድ ወድቆ ጩኸት በበዛበት እሳት የጎረሰ እሳት አስተዋሉ ያበሻን ጀግንነት ከካሳ ተማሩ፡፡ አሁንም ተነሱ ! ግብረ ቴዎድሮሶች የድሮ ስርአት ዳግም ናፋቂዎች የተቆጣ ስሜት ከፈላ ደም ጋር ባንድነት ቀይጠው ሀውልቱን ገነቡ በደም ባጥንታቸው ካዚያማ! አፍራሽ ገባውና መሰረቱን ሊጥል ሌት ተቀን ሲለፋ ተቆጣ ደማቸው ቤታቸው ሲገፋ ክብራቸው ሲጠፋ የነፍጠኛ ልጆች ነፍጥ ይዘው ተነሱ ያባታቸውን ክብር ዳግም ሊመልሱ (ዘላለም በላይነህ)
Subscribe to:
Comments (Atom)
ጠወለገች አሉ!!
ጠወለገች አሉ!! አባይ ወዲያ ማዶ ከተከዜ ግርጌ የበቀለች ወይን የቆመች ብሳና ጠወለገች አሉ ሰው አጣለችና!!! የግዮን አገር ሰው ታሪክን የሰራ በተወለደበት እንዴት ...
-
፠፠፠ የተኮሳተረ አገሩን የሚያልም፥ ተስፋ የገመደ ግንባር ይታየኛል፡፡ እንደራሱ ጸጉር ነፍጥና ጀግነነት፥ ወኔና ወንድነት አጣምሮ ገምዷል፡፡ ሎሚታ ያስጌጠው የእሳት ጎራዴ ፥ ካፎቱ ተመዝዞ ከሰገባው ...
-
ህግ እንደተርጔሚው …..ተብሎ ከተጣፈ ገመና ሼፋኜን ቤቴን ልስራ ባለ……ህግ ከተላለፈ መዝግቡኝ ናሳዎች ….ወደማርስ ልሄድ ነው ከምድር አልችልም ….መሬት ለመንግስት ነው!!! ‹‹‹‹‹‹‹‹‹እዩት ይሄ...
-
ጠወለገች አሉ!! አባይ ወዲያ ማዶ ከተከዜ ግርጌ የበቀለች ወይን የቆመች ብሳና ጠወለገች አሉ ሰው አጣለችና!!! የግዮን አገር ሰው ታሪክን የሰራ በተወለደበት እንዴት ...


