Tuesday, 16 January 2018

ወደማርስ ልሄድ ነው




ህግ እንደተርጔሚው …..ተብሎ ከተጣፈ
ገመና ሼፋኜን ቤቴን ልስራ ባለ……ህግ ከተላለፈ
መዝግቡኝ ናሳዎች ….ወደማርስ ልሄድ ነው
ከምድር አልችልም ….መሬት ለመንግስት ነው!!!
‹‹‹‹‹‹‹‹‹እዩት ይሄን ዘማኝ!!!!!
ፍርድ ሲገመድል…… ስልጣኑን ሲጋፋ
መሬት ከፈጣሪ የሚለዉ ቀረና ……መሬት ለመንግስት ነው ብሎልህ አረፋ İİ

አፈር እና ውሃ……… አየርና ፀሐይ
እኩል የታደለን ……ቢሆንም ከእርሱ ላይ
ዛሬ ፈረሰና ……ታሪክ ተቀየረ
ከመንግስት ሆነና ……ካምላክ ሚለዉ ቀረİİ

ከወንዙ ዳርቻ ‹‹‹‹ከፎቁ ታዛ ስር›››››
ከነገመናዋ የቀባኋት ምርጊት…… የቆመች በአፈር
በቀን የመጣ ጅብ ……ገፍቶ ካፈረሳት
ኧረ እናቴ ትሙት!!!!!  ሚስቴንም ይዉሰዳት İİ

ወገን ከወገኑ……… እየተበላላ
ሰው ከስልጣኑ ጋር…… ሁሌ እየተጣላ
ቂም የነገሰባት …… ባቢሎን ሆነናል
በጥንስስ አለም ላይ…… ተንጋለን ወድቀናል፡፡

የቦለቲካ መርዝ…. በዲስኩር ተገምዶ
እልፍ ዘመን ሲያልፍ……ብዙ ዘመን ሄዶ
‹‹‹አፍላጋት ወረሰን›››… አብዮት ፈነዳ
የደም ጎርፍ ወሰደን …..ምድር ገባች እዳ
ሰማይ እንደጣራ… ዝቅ አለ ተከፍቶ
በዝናቡ ፋንታ …..የሰዉን ደም አይቶ
‹‹‹‹‹‹‹እዩት ይሄን ዘማኝİİİ
በኪነት ምህዳር……. ያልታጠነዉ ጣዖት
ያ’ብሮነት ገበታ …ያስጠላዉ ተሩፋት
እንደአለማወቁ …ቀድሞ በማወቁ
ጭካኔን አንግሶ  ….ፍትህን ማራቁ፡፡

ስለዚህ ወገኔ!!!!!!

ህግ እንደተርጔሚዉ….. ተብሎ ከተፃፈ
ገመና ሼፋኙን ቤቴን ልስራ ባለ ……..ህግ ከተላለፈ
ተሰነባበቱኝ ወደማርስ …..ልሄድ ነው
ከምድር አልችልም….. መሬት ለመንግስት ነው፡፡

እዩት ይሄን አዳም!!!!!  ፍርድ ሲገመድል ስልጣኑን ሲጋፋ
ባልተፈቀደለት…. በበለስ ሲጠፋ
‹‹‹‹የገነት ዉሃ ልጅ የአባይ ልጅ ሲገፋ››››
መሬት ከፈጣሪው የሚለውን ፍቆ መሬት ለመንግስት ነዉ ብሎልህ አረፋİİİİİİ

ህግ እንደተርጔሚዉ…. ነዉ ከተባባሉ
መንግስት ማለት ህዝብ ቢሆንም ግን ቅሉ
እንግዲህ ተርጉመዉ ‹‹‹አንተ ባለቅኔ ›››
እያመድህ ያለኸ በበረሀዉ ጠኔ
(ዘላለም በላይነህ)




No comments:

Post a Comment

ጠወለገች አሉ!!

ጠወለገች አሉ!! አባይ ወዲያ ማዶ ከተከዜ ግርጌ   የበቀለች ወይን የቆመች ብሳና ጠወለገች አሉ ሰው አጣለችና!!! የግዮን አገር ሰው ታሪክን የሰራ   በተወለደበት እንዴት ...