Wednesday, 17 January 2018

-------የስላቅ ዋ ! ዜማ İİ----------







----የስላቅ ! ዜማ İİ----------
----------//----------------
እንኳን አደረሰህ--- አትበይኝ ፍቅሬ----እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል --- የደማው ውስጠቴ---- የቆሰለው ቁስሌ፡፡
-------//-----------
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን ደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
---------*****----------
(
ስሚኝማ ውዴ)


ለዘመኑ ብስራት ---- በባዕል ! ዜማ
ባልነበረ ታሪክ --- ግፋቸው ሲሰማ
መድፍ ይተኩሳሉ----በመለከት ፋንታ
ለድንበር የሚሞት-- ወታደር ይመስል-- የጦር መሪ ጋንታ
(---

------

---------
----ይቀጥላል)
በማታለል ዘዬ----- በቸከ ቅላፄ
ዘወትር ሲያላዝን -----ደም የዋጠው አፄ
ለጀብጀቦ አጎብዳጅ------ ለቸከ ህሌና
መድፍ እየተኮሱ------ ሊያደርቁን ነውና፡፡
---//-----
(
አይገርም የኔ ውድ!!)
ግዳይ እንደጣለ--- እንደ አባይ ልጅ አዳኝ
እንደ አባ ታጠቁ--- እንደ አንበሳ ገዳይ
ሊላዝንብን ነው-- ባላየነው እውነት-- በማይገባን ዜማ
በማታለል ቅኔ --በለበጣ ቃላት----- ልባችን ሊደማ፡፡
(
ተመልከች የኔ ውድ)
የደርሶ መልስ --አመት መከራ--- ሊያበስረን
የበግ ደም ሰውቶ-- በየአደባባዩ---- እንቁ ጣጣሽ ሊለን
ካራውን ይስላል------በጎቹን ሰውቶ--- ለበጎች ሊየበላን፡፡
(
**** እንግዲ----)
የበግ ስጋ ለበግ-- በየትኛው ሀገር -- --- ያውቃል
ማንስ ይሄን ርጎ---ለህዝበ አዳም ልጆች--- አስደስቶ ውሏል
ባላየነው እውነት ባልሰማነው ዜማ ሀሴት ይስተጋባል???
*********//*********
(
ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ)
እንኳን አደረሰህ ---አትበይኝ ፍቅሬ-----እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል -- የደማው ውስጠቴ--- የቆሰለው ቁስሌ
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን አደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
(
ምክንያቱም---- ውዴ)
! ዜማን ደግሰው ----ለአዲስ አመት ብስራት
እየተሳለቁ ------በሞተ ማንነት
አድምጡ ይሉናል--- ቅኝት አልባ ዘፈን
ቁና ሙሉ ስቃይ--- መከራን ሲያበስሩን
ደስታነው ብለው-- !ዜማን ሲነግሩን
******///********
እናሄን እያየሽ--- የምን መልካም ዘመን--- የምን አዲስ አመት
ለገደሉት ውስጤ ------ሞት ሲደገስለት?
(
ምን አልባት የኔ ውድ)
ኤልያስ ከመጣ----- ደመና ተላብሶ 
የነሱን !! ዜማ---- ድግስ አስቀይሶ 
አዲስ ዘመን ካየን--- ከሞታችን ጀርባ
ያን ጊዜ ትያለሽ------- በተቀኜ ዜማ 
ምን አልባት የኔ ውድ
ዝናቡ ካባራ ------ደምን የሚያዘንበው 
መድፉን በመለከት----- ቀይሮ ካየነው
አዲስ አመት መባል------ ለኔ ያን--- ጊዜ ነው፡፡
(
ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ)
እንኳን አደረሰህ ---እንዳትይኝ ዛሬ -እርግማን ነው ለኔ
ጠፈፍ እንኳ ሳይል -- የደማው ውስጠቴ--- የቆሰለው ቁስሌ
አዲስ በሚል ሰበብ ----ሞት ሲደገስልኝ
እንኳን አደረስህ ---አትበይኝ ፍቅሬ--- ይልቅ አልቅሽልኝ፡፡
(
ዜዶ ነኝ የብእር አይኖች ከፈቱ)



No comments:

Post a Comment

ጠወለገች አሉ!!

ጠወለገች አሉ!! አባይ ወዲያ ማዶ ከተከዜ ግርጌ   የበቀለች ወይን የቆመች ብሳና ጠወለገች አሉ ሰው አጣለችና!!! የግዮን አገር ሰው ታሪክን የሰራ   በተወለደበት እንዴት ...